መድኃኒዓለም (የዓለም መድኃኒት )
የ አግዚአብሔር ልጅ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምን ለማዳን ቃል ኪዳን ገብቶለት ስለነበር ያን ቃል ኪዳኑን ጠብቆ ከሰማየ ሰማይ ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ስጋን ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ተወልዶ አምላክ ነኝ ቶሎ ልደግ ሳይል እንደ ሕፃናት ጥቂት በጥቂት አድጎ ፴ ዓመት ሲሞላው ማስተማር ጀመረ።፫ዓምት ከ፫ ወር ዙሮ ካስተማረ በኋላ ለአዳም የገባለት 5500 ዘመን ሲፈፀም አይሁድ ሰቅለው ገደሉት።በሥጋ ወደ መቃብር በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን ባዷዋን አስቀርቶ በዝያ የነበሩትንም ነፍሳት በሙሉ ወደ ገነት አስገብቷቸዋል ።በሞቱ ሞቱን ሸሮ በሶስተኛው ቀን ከሙታን ተነስቶ ፵ ቀን ካስተማረ በኋላ በ ፵ኛው ቀን አርጉአል።በሞቱ አለምን ስላዳነም መድኃኒዓለም ተባለ ።
መድኃኒዓለም አዳነን
መድኃኒዓለም አዳነን
መድኃኒዓለም አዳነን በማይሻር ቃሉ አምላካቺን አዳነን በማይሻር ቃሉ(2)
ደስ ይበለን (፪)እልል በሉ (፪)አዳነን በማይሻር ቃሉ(2)
ደስ ይበለን (፪)እልል በሉ (፪)አዳነን በማይሻር ቃሉ(2)
ከመድኃኒዓለም ረድዔት በረከት ያሳትፈን።መድኃኒዓለም በመንግስቱ ያስበን።አሜን።
ይቆየን ።
No comments:
Post a Comment