ንብረት አጣሁ ብለህ
በሃሳብ አትለቅ ፣
ንብረት ጤንነት ነው
ፀጋህን አትናቅ፣
መልክ የለኝም ብለህ
እንዳትዘናጋ ፣
በአምሳሉ ፈጥሮሃል
አልፋና ኦሜጋ፣
ስልጣን ስለሌለህ
ልብህ እንዳያዝን፣
ስልጣን ተሰጥቶሃል
የአምላክ ልጅ ለምሆን፣
ወገን የለኝ ብለህ
ምን ያስጨንቅሃል
ከቅዱሳን ጋራ
ባለ ሀገር ሆነሃል።
No comments:
Post a Comment